መድሃኒቶች የአእምሮ መዛባትን እና ህመሞችን በማከም ረገድ ሚና ሊጫወቱ ይችላሉ፤ እናም ብዙ ጊዜ ከሳይኮቴራፒ፣ ከአንጎል ማነቃቂያ ቴራፒ እና መሰል የሕክምና ዘዴዎች ጋር በማጣመር ጥቅም ላይ ይውላሉ። መድሃኒቶቹ ሰዎችን በተለያየ መንገድ ሊጎዱ ይችላሉ፤ እናም ለታማሚው በጣም ውጤታማ እና አነስተኛ የጎንዮሽ ጉዳት ያለውን መድሃኒት ለማግኘት ብዙ ሙከራዎች ይደረጋሉ። ሰዎች ፍላጎቶቻቸውን እና የሕክምና ሁኔታቸውን የሚያሟላ የሕክምና ዕቅድ ለማዘጋጀት ከጤና እንክብካቤ አቅራቢ ወይም ከአእምሮ ጤና ባለሙያ ጋር አብረው መሥራት ያስፈልጋቸዋል።
ስለ መድሃኒቶች የሚወጡ መረጃዎች በየጊዜው ይዘምናሉ። ቅርብ ጊዜ ስለ ወጡ ማስጠንቀቂያዎች፣ ስለ መድኃኒት መመሪያዎች እና አዲስ በሳይንስ ተረጋግጠው ተቀባይነት ስላገኙ መድኃኒቶች መረጃ ለማግኘት የ U.S የምግብ እና የመድኃኒት አስተዳደር (FDA) የመድኃኒት መመሪያ ድረ-ገጽን ይጎብኙ። እንዲሁም The MedlinePlus Drugs፣ Herbs እና Supplements የተሰኙ ድረ-ገጽጾችም ስለ መድሐኒቶች፣ ስለጎንዮሽ ጉዳቶች፣ እና ከFDA ስለሚወጡ ማስጠንቀቂያዎች መረጃዎችን ይሰጣሉ።
ይህ ድረ-ገፅ ስለአይምሮ ጤና መድሀኒቶች መሰረታዊ መረጃዎችን ይሰጣል። ነገር ግን ስለ ሁሉም መድሃኒቶች መረጃ ስለማይሰጥ የህክምና ውሳኔዎችን ለመወሰን እንደ መመሪያ ልንጠቀመው አይገባም።
This post is also available in:
English (እንግሊዝኛ)
