Skip to content
Home » የአእምሮ መታወክ » ሳይኮቲክ በሽታዎች » ስኪዞፈሪንያ

ስኪዞፈሪንያ

ስኪዞፈሪንያ ምንድን ነው?

ስኪዞፈሪንያ አንድ ሰው በሚያስብበት፣ በሚሰማው እና በባህሪው ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ የሚያሳድር ከባድ የአእምሮ ሕመም ነው። ስኪዞፈሪንያ ያለባቸው ሰዎች ከሚያሳዩት ባህርይ የተነሳ ሰዎቹ ከገሀዱ አለም እውነታ ጋር ያላቸውን ግንኙነት ሙሉ በሙሉ የተቋረጠ ይመስላል፤ ይህም ለእነሱ፣ ለቤተሰባቸው እና ለጓደኞቻቸው ትልቅ ጭንቀት ይፈጥራል። ስኪዞፈሪንያ ያለባቸው ሰዎች በተለመደው የዕለት ተዕለት ተግባራት መሳተፍ እጅግ ይከብዳቸዋል። ነገር ግን ለስኪዞፍሬኒያ ውጤታማ የሆኑ ህክምናዎች አሉ። ወጤታማ ሕክምና የሚያገኙ ታማሚዎች ጤናቸው ተመልሶ በትምህርት ቤት ወይም በሥራ ገበታቸው ውጤታማ ሊሆኑ እና በግል ህይወታቸውም ደስተኛ እና ነጻ ሊሆኑ ይችላሉ።

የስኪዞፈሪንያ ምልክቶች ምን ምን ናቸው?

የስኪዞፈሪንያ ምልክቶች ሲታዩ መለየት እና በተቻለ ፍጥነት እርዳታ መፈለግ አስፈላጊ ነው። ስኪዞፈሪንያ ያለባቸው ሰዎች በሽታው እንዳለባቸው የሚለየው ብዙውን ጊዜ ከ16 እስከ 30 ዓመት ባለው የዕድሜ ክልል ውስጥ ነው፤ በሽታው ለመጀመሪያው ግዜ ከተገለጠ በኋላ። በሽታው ለመጀመሪያውን ጊዜ ከተገለጠ በኋላ በተቻለ ፍጥነት ህክምና መጀመር ለፈወስ እጅግ ወሳኝ እርምጃ ነው። ይሁን እንጂ፣ በሽታው ለመጀመሪያ ጊዜ ከመገለጡ በፊትም በአስተሳሰብ፣ በስሜቶች እና በማህበራዊ ተግባራት ላይ አንዳንድ ለውጦች ቀስ በቀስ እንደሚታዩ ጥናቶች ያሳያሉ። ህጻናት እና ታዳጊዎች በኪዞፈሪንያ የመጠቃት እድላቸው እጅግ አነስተኛ ነው።

የስኪዞፈሪንያ ምልክቶች ከሰው ሰው ሊለያዩ ይችላሉ ነገር ግን በአጠቃላይ በሦስት ዋና ዋና ጎራዎች ይመደባሉ፦ ሳይኮቲክ፣ አሉታዊ እና ግንዛቤአዊ።

ሳይኮቲክ ምልክቶች በግለሰቡ አስተሳሰብ፣ ድርጊት እና አለምን በሚመለከትበት መንገድ ላይ የሚፈጠሩ ለውጦችን ያጠቃልላል። ሳይኮቲክ ምልክቶች የሚታይባቸው ሰዎች ነባራዊውን አለም የሚመለከቱበት መንገድ ከሌሎች ሰዎች የተለየ ሊሆን እና ዓለምን በተዛባ መንገድ ይመለከታሉ። አንዳንድ ሰዎች ላይ እነዚህ ምልክቶች በየጊዜው እየመጡ ይሄዳሉ። በሌሎች ላይ ደግሞ ምልክቶቹ በጊዜ ሂደት በቋሚነቱ ይጸናሉ። የሳይኮቲክ ምልክቶች የሚከተሉትን ያካትታሉ፦

  • Hallucinations: Hallucinations ማለት አንድ ሰው በእውኑ አለም የሌሉ ነገሮችን ሲያይ፣ ሲሰማ፣ ሲሸተው፣ ሲቀምስ ወይም ሲሰማው ነው። በእውን የሌለን ድምጽ መስማት ስኪዞፍሬኒያ ባለባቸው ሰዎች ላይ የሚታይ የተለመደ ምልክት ነው። በእውን የሌለ ድምጽ የሚሰሙ ሰዎች ቤተሰብ ወይም ጓደኞች ይህንን ችግር ከማስተዋላቸው አስቀድሞ ለረጅም ጊዜ ሊሰሙ ይችላሉ።
  • Delusion: Delusion ማለት አንድ ሰው ከእውነት የራቁ እና ለሌሎች ሰዎች ምክንያታዊ ያልሆኑ ጠንካራ እምነቶች ሲኖሩት ነው። ለምሳሌ፣ Delusion ውስጥ ያሉ ሰዎች በራዲዮ እና በቴሌቭዥን የሚሰሩ ሰዎች የተለየ ምላሽ የሚሹ መልዕክቶችን እንደሚልኩላቸው፣ ወይም አደጋ ላይ እንደሆኑ ወይም ሌሎች ሰዎች እነሱን ለመጉዳት እየሞከሩ እንደሆነ ሊያስቡ ይችላሉ።
  • Thought disorder፦ ይህ ደግሞ አንድ ሰው ያልተለመደ ወይም ምክንያታዊ ያልሆነ አስተሳሰብ ሲኖረው ነው። Thought disorder ያለባቸው ሰዎች ሃሳባቸውን እና ንግግራቸውን ለማደራጀት ሊቸገሩ ይችላል። ይህ ችግር ያለበት ሰው አንዳንድ ጊዜ በሃሳብ መሀል ማውራት ሊያቆም፣ ከርዕስ ወደ ርዕስ ሊዘል፣ ወይም ትርጉም የሌላቸውን ቃላት ሊፈጥር ይችላል።
  • Movement disorder: ይኼ፣ አንድ ሰው ያልተለመደ የሰውነት እንቅስቃሴ እንዲያሳይ የሚያደርግ እክል ነው። ችግሩ ያለባቸው ሰዎች አንዳንድ እንቅስቃሴዎችን ብዙ ጊዜ ይደግማሉ።

አሉታዊ ምልክቶች ተነሳሽነት ማጣት፣ የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ ላይ ፍላጎት ወይም ደስታ ማጣት፣ ከማህበራዊ ህይወት መራቅ፣ የስሜት መረበሽ እና የመደበኛ ህይወት መረበሽ ናቸው።

አሉታዊ ምልክቶች የሚከተሉትን ያካትታሉ፦

  • ማቀድ እና ያንን እቅድ ለመተግበር መቸገር፤ ለምሳሌ ገበያ ሄዶ እቃ መግዛት ሊሆን ይችላል።
  • አንድን ነገር መጠበቅ እና ኋላም መደሰት ያለመቻል ችግር
  • ዝግ ባለ ድምጽ ለብቻ ማውራት እና ወስን የሆኑ የፊት ገጽታዎችን ማሳየት
  • ማህበራዊ ግንኙነቶችን ማስወገድ ወይም በማህበራዊ ግንኙነቶች ጤነኛ ያልሆኑ ባህርያትን ማሳየት።
  • ከፍተኛ ድካም እና ብዙ ጊዜ በእንቅስቃሴ ማሳለፍ። ከባድ በሆኑ ሁኔታዎች ግለሰቡ ለተወሰነ ጊዜ  መንቀሳቀስ ወይም መናገርን ሊያቆም ይችላል፤ ይህ ደግሞ ካታቶኒያ ተብሎ የሚጠራ ያልተለመደ ችግር ነው።

እነዚህ ምልክቶች አንዳንድ ጊዜ የድባቴ ወይም የሌሎች የአእምሮ ሕመሞች ምልክቶች ናቸው።

የግዛቤ (ኮግኒቲቭ) ምልክቶች የትኩረት እና የማስታወስ ችግርን ያካትታሉ። እነዚህ ችግሮች ተጠቂው ግለሰብ ውይይቶችን በሚገባ መከታተል፣ አዳዲስ ነገሮችን መማር ወይም ቀጠሮ ማስታወስ እንዲከብደው ያደርጋሉ። የአንድ ሰው የአአምሮ (ኮግኒቲቭ) ተግባር ደረጃ የግለሰቡን ሁኔታ ለመገምገም ወሳኝ ከሆኑ ነገሮች አንዱ ነው። ሐኪሞች የተለያዩ ዘዴዎችን በመጠቀም የሰዎችን የአአምሮ (ኮግኒቲቭ) ሁኔታ ይገመግማሉ።

የግንዛቤ (ኮግኒቲቭ) ምልክቶች የሚከተሉትን ያካትታሉ፦

  • ስለ አንድ ነገር ውሳኔ ለመስጠት መረጃዎችን ለመገምገም መቸገር
  • አንድን መረጃ ካገኙ በኋላ መረጃውን ጥቅም ላይ ለማዋል መቸገር
  • በአንድ ነገር ላይ ትኩረት ለማድረግ መቸገር

የበሽታ መቆጣጠር እና መከላከል ማእከል (CDC)፣ ዲፕሬሽን እና ስኪዞፈሪንያ ጨምሮ አንዳንድ የአእምሮ ሕመሞች በኮቪድ-19 የተጠቁ ሰዎች በጠና እንዲታመሙ ያደርጋሉ። እርዳታ ስለማግኘታ እና የአአምሮ ጤና ሀኪም ለማግኘት የበለጠ ይማሩ።

ሁከት የመፍጠር አደጋ

አብዛኛዎቹ ስኪዞፈሪንያ ያለባቸው ሰዎች ሀካተኛ አይደሉም። በአጠቃላይ፣ ስኪዞፈሪንያ ያለባቸው ሰዎች በሽታው ከሌላቸው ሰዎች ይልቅ በሌሎች የመጎዳት ዕድላቸው ከፍተኛ ነው። ስኪዞፈሪንያ ያለባቸው ሰዎች ተገቢ ህክምና ካላገኙ ራሳቸውን የመጉዳት እና በሌሎች ላይ ጥቃት የመሰንዘር ዕድላቸው ከፍተኛ ነው። ምልክቱ ያለባቸው ሰዎች በተቻለ ፍጥነት ህክምና እንዲያገኙ መርዳት እጅግ አስፈላጊ ነው።

ስኪዞፈሪንያ እና dissociative identity disorder

ምንም እንኳን አንዳንድ ምልክቶች ላይ ላዩን ሲታዩ ተመሳሳይ ቢመስሉም፣ ስኪዞፈሪንያ እና dissociative identity disorder የተለያዩ ናቸው። ይህ ችግር ያለባቸው ሰዎች በተለያዩ ሁኔታዎች የሚገለጡ ሁለት ወይም ከዚያ በላይ ማንነቶች ወይ ባህርያት አሏቸው።

ለስኪዞፈሪንያ የሚያጋልጡ ምክንያቶች ምንድን ናቸው?

አንድ ሰው ለስኪዞፈሪንያ የመጋለጥ እድሉን ከፍ ሊያደርጉ የሚችሉ ብዙ ምክንያቶች አሉ።

ዘረመል(gene)፦ ስኪዞፈሪንያ አንዳንድ ጊዜ በዘር ይተላለፋል። ነገር ግን፣ ከአንድ ቤተሰብ አንድ ሰው ስኪዞፈሪንያ አለበት ማለት ሌሎች የቤተሰብ አባላትም ስኪዞፍሬኒያ ያጋጥማቸዋል ማለት አይደለም። ጥናቶች እንደሚያሳዩት ብዙ የተለያዩ ጂኖች የአንድን ሰው ለስኪዞፈሪንያ የመጋለጥ እድል ከፍ ሊያደርጉ ይችላሉ፤ ነገር ግን አንድ ጂን በራሱ በሽታውን ሊያመጣ አይችልም።

አካባቢ፡ ጥናቶች እንደሚያሳዩት ዘረመል እና የግለሰቡ አከባቢ እና ያለፈበት የህይወት መንገድ ተጣምረው ለስኪዞፈሪንያ ምክንያት ሊሆኑ ይችላሉ። አካባቢ በድህነት ውስጥ መኖርን፣ አስጨናቂ ወይም አደገኛ አካባቢን፣ እና ከመወለዳቸው በፊት ለተለያዩ ቫይረሶች ወይም ለአመጋገብ ችግሮች መጋለጥን ያካትታል።

የአንጎል መዋቅር እና ተግባር፦ ስኪዞፈሪንያ ያለባቸው ሰዎች በአንዳንድ የአንጎል ክልሎች መጠን እና በአንጎል ክልሎች መካከል ባለው ግንኙነት ከሌሎች ሰዎች ልዩነት ሊኖራቸው እንደሚችል ጥናቶች ያሳያሉ። ከእነዚህ የአንጎል ልዩነቶች መካከል አንዳንዶቹ ከመወለዳቸው በፊት የሚፈጠሩ ናቸው። ተመራማሪዎች የአንጎል መዋቅር እና ተግባር ከስኪዞፈሪንያ ጋር እንዴት እንደሚዛመድ በተሻለ ለመረዳት ምርምር እያደረጉ ነው።

ስኪዞፈሪንያ እንዴት ይታከማል?

ስኪዞፈሪንያ እንዴት ይታከማል?

አሁን ያሉት የስኪዞፈሪንያ ህክምናዎች ሰዎች የበሽታውን ምልክቶች እንዲቆጣጠሩ፣ የእለት ተእለት ተግባራቸውን እንዲያሻሽሉ እና የግል ህይወት ግቦቻቸችን እንዲያሳኩ በመርዳት ላይ ያተኩራሉ፤ ለምሳሌ ትምህርትን ማጠናቀቅ፣ ስራ ላይ መትጋት እና ከሰዎች ጋር ሰላማዊ ግንኙነት ማዳበር።

ሳይኮሶሻል ሕክምናዎች ሰዎች ለየዕለት ተግዳሮቶች መፍትሄ እንዲያገኙ እና ትምህርት ቤት ሲማሩ፣ ሲሰሩ እና ከሰዎች ጋር ባላቸው ግንኙነት ምልክቶችን እንዲቆጣጠሩሩ ይረዷቸዋል። እነዚህ ሕክምናዎች ብዙውን ጊዜ ከአንቲሳይኮቲክ መድኃኒቶች ጋር አብረው ጥቅም ላይ ይውላሉ። በሳይኮሶሻል ህክምና በመደበኛነት የሚሳተፉ ሰዎች ላይ የበሽታው ምልክቶች እንደገና የመከሰት ወይም ሆስፒታል ወስጥ ተኝተው እንዲታከሙ የመደረግ እድላቸው አነስተኛ ነው።

የዚህ ዓይነቱ ሕክምና ምሳሌዎች የሚከተሉት ናቸው፦ ኮግኒቲዥ ቤሄቨራል ቴራፒ፣ የባህሪ ክህሎት ስልጠና፣ እና የግንዛቤ ማሻሻያ ቴራፒ።

ትምህርት እና ድጋፍ

የትምህርት ፕሮግራሞች ስለ ስኪዞፈሪንያ ምልክቶች፣ የሕክምና አማራጮች እና በበሽታው የተጠቁ የቅርብ ሰዎችን የመርዳት ስልቶችን ለማስተማር ይረዳሉ። እነዚህ ፕሮግራሞች የበሽታው ተጠቂ ግለሰብ ጓደኞች እና ቤተሰብ ጭንቀታቸውን እንዴት እንደሚቆጣጠሩ፣ ችግሩን የመቋቋም ችሎታቸውን እንዲያሳድጉ እና ድጋፍ የመስጠት ችሎታቸውን እንዲያጠናክሩ ያግዛሉ። የአእምሮ ህመምን የመቆጣጠር ብሔራዊ ጥምረት ስለ ደጋፊ ቡድኖች እና ስለ ትምህርት የበለጠ መረጃ ይሰጣል።

የተቀናጀ ልዩ እንክብካቤ

የተቀናጀ ልዩ እንክብካቤ ፕሮግራሞች የመጀመሪያ ደረጃ ስኪዞፍሬኒያ ያለባቸው ሰዎች ወይም በሽታው ገና እየታየባቸው ያለ ሰዎች እንዲያገግሙ የማድረግ ስራ ላይ ያተኮሩ ፕሮግራሞች ናቸው። ይህንን ስራ የጤና እንክብካቤ አቅራቢዎች እና ስፔሻሊስቶች በመጣመር ይሰራሉ። ህክምናውም ሳይኮቴራፒ፣ መድሀኒት፣ የስራ እና የትምህርት ድጋፍ፣ እና የቤተሰብ ትምህርት እና ድጋፍን ያካትታል። የሕክምና ቡድኑ በተቻለ መጠን የቤተሰብ አባላትን እና ግለሰቡን በማሳተፍ የሕክምና ውሳኔዎችን ለመወሰን እና ህክምናውን ለማሳለጥ ይጥላል።

ከተለመደው የህክምና አሰጣጥ ጋር ሲነጻጸር፣ የተቀናጀ ልዩ እንክብካቤ ምልክቶችን ለመቀነስ፣ የህይወት ጥራትን ለማሻሻል እና በስራ ወይም በትምህርት ቤት ውስጥ ተሳትፎን ለመጨመር የበለጠ ውጤታማ ነው።

አንቲሳይኮቲክ መድኃኒቶች

አንቲሳይኮቲክ መድሐኒቶች የሳይኮቲክ ምልክቶችን ኃይለኝነታቸው እንዲቀንስ እና ብዙ ጊዜ እንዳይከሰቱ ለማድረግ ይረዳሉ። እነዚህ መድሃኒቶች ብዙውን ጊዜ በየቀኑ በመድሃኒት ወይም በፈሳሽ መልክ ይወሰዳሉ። አንዳንድ አንቲሳይኮቲክ መድኃኒቶች በወር አንድ ጊዜ ወይም ሁለት ጊዜ በመርፌ ይሰጣሉ።

በተለመደው አንቲሳይኮቲክ መድሃኒቶች የአንድ ሰው ምልክቶች ካልተሻሻሉ ክሎዛፒን ሊታዘዝለት ይችላል። ክሎዛፒን የሚወስዱ ሰዎች ከ1 እስከ 2 ፐርሰንት ታካሚዎች ላይ ሊከሰት የሚችለውን አደገኛ የጎንዮሽ ጉዳት ለመፈተሽ መደበኛ የደም ምርመራ ማድረግ አለባቸው።

ሰዎች አንቲሳይኮቲክ መድሐኒቶች ሲወስዱ የተለያዩ ምላሾችን ያሳያሉ። ማንኛውንም የጎንዮሽ ጉዳት ለሀኪም ማሳወቅ አስፈላጊ ነው። ብዙ ሰዎች አንቲሳይኮቲክ መድኃኒቶችን ሲወስዱ የክብደት መጨመር፣ የአፍ መድረቅ፣ እረፍት ማጣት እና የመሳሰሉ የጎንዮሽ ጉዳቶች ያጋጥሟቸዋል። ከእነዚህ የጎንዮሽ ጉዳቶች መካከል አንዳንዶቹ በጊዜ ሂደት ሊጠፉ ይችላሉ። ሌሎች ደግሞ ሊቆዩ ይችላሉ።

ምርጡን የመድኃኒት ዓይነት ወይም የመድኃኒት ጥምረት እና ትክክለኛውን ዶዝ ለመወሰን ሐኪም እና ታካሚዎች ተባብረው መስራት አለባቸው። ስለ አንቲሳይኮቲክ መድሐኒና የቅርብ ጊዜ መረጃ ለማግኘት ሀኪሞችን ያነጋግሩ ወይም የዩኤስ የምግብ እና የመድኃኒት አስተዳደር (ኤፍዲኤ) ድረ-ገጽን ይጎብኙ።

ሳይኮሶሻል ሕክምና

ሳይኮሶሻል ሕክምናዎች ሰዎች ለየዕለት ተግዳሮቶች መፍትሄ እንዲያገኙ እና ትምህርት ቤት ሲማሩ፣ ሲሰሩ እና ከሰዎች ጋር ባላቸው ግንኙነት ምልክቶችን እንዲቆጣጠሩሩ ይረዷቸዋል። እነዚህ ሕክምናዎች ብዙውን ጊዜ ከአንቲሳይኮቲክ መድኃኒቶች ጋር አብረው ጥቅም ላይ ይውላሉ። በሳይኮሶሻል ህክምና በመደበኛነት የሚሳተፉ ሰዎች ላይ የበሽታው ምልክቶች እንደገና የመከሰት ወይም ሆስፒታል ወስጥ ተኝተው እንዲታከሙ የመደረግ እድላቸው አነስተኛ ነው።

የዚህ ዓይነቱ ሕክምና ምሳሌዎች የሚከተሉት ናቸው፦ ኮግኒቲዥ ቤሄቨራል ቴራፒ፣ የባህሪ ክህሎት ስልጠና፣ እና የግንዛቤ ማሻሻያ ቴራፒ።

ትምህርት እና ድጋፍ

የትምህርት ፕሮግራሞች ስለ ስኪዞፈሪንያ ምልክቶች፣ የሕክምና አማራጮች እና በበሽታው የተጠቁ የቅርብ ሰዎችን የመርዳት ስልቶችን ለማስተማር ይረዳሉ። እነዚህ ፕሮግራሞች የበሽታው ተጠቂ ግለሰብ ጓደኞች እና ቤተሰብ ጭንቀታቸውን እንዴት እንደሚቆጣጠሩ፣ ችግሩን የመቋቋም ችሎታቸውን እንዲያሳድጉ እና ድጋፍ የመስጠት ችሎታቸውን እንዲያጠናክሩ ያግዛሉ። የአእምሮ ህመምን የመቆጣጠር ብሔራዊ ጥምረት ስለ ደጋፊ ቡድኖች እና ስለ ትምህርት የበለጠ መረጃ ይሰጣል።

የተቀናጀ ልዩ እንክብካቤ

የተቀናጀ ልዩ እንክብካቤ ፕሮግራሞች የመጀመሪያ ደረጃ ስኪዞፍሬኒያ ያለባቸው ሰዎች ወይም በሽታው ገና እየታየባቸው ያለ ሰዎች እንዲያገግሙ የማድረግ ስራ ላይ ያተኮሩ ፕሮግራሞች ናቸው። ይህንን ስራ የጤና እንክብካቤ አቅራቢዎች እና ስፔሻሊስቶች በመጣመር ይሰራሉ። ህክምናውም ሳይኮቴራፒ፣ መድሀኒት፣ የስራ እና የትምህርት ድጋፍ፣ እና የቤተሰብ ትምህርት እና ድጋፍን ያካትታል። የሕክምና ቡድኑ በተቻለ መጠን የቤተሰብ አባላትን እና ግለሰቡን በማሳተፍ የሕክምና ውሳኔዎችን ለመወሰን እና ህክምናውን ለማሳለጥ ይጥላል።

ከተለመደው የህክምና አሰጣጥ ጋር ሲነጻጸር፣ የተቀናጀ ልዩ እንክብካቤ ምልክቶችን ለመቀነስ፣ የህይወት ጥራትን ለማሻሻል እና በስራ ወይም በትምህርት ቤት ውስጥ ተሳትፎን ለመጨመር የበለጠ ውጤታማ ነው።

አሰርቲቪ የማህበረሰብ ህክምና

አሴርቲቭ የማህበረሰብ ህክምና ወይም A.C.T፣ ብዙ ጊዜ ሆስፒታል የሚገቡ ወይም ጨረሶ ጎዳና የመውጣት አደጋ ላለባቸው የስኪዞፍሬኒያ ታማሚዎች በተለየ ሁኔታ የተነደፈ ህክምና ነው። ACT ብዙውን ጊዜ፣ በማህበረሰቡ ውስጥ ላሉ ታማሚዎች፣ አብረው በሚሰሩ የህክምና ባለሙያዎች ቡድን የሚሰጥ ህክምና ነው።

የአደንዛዥ ዕፅ እና የአልኮል ሱስ ላለባቸው ሰዎች የሚሰጥ ህክምና።

ስኪዞፈሪንያ ያለባቸው ሰዎች ብዙ ግዜ በአደንዛዥ ዕፅ እና በአልኮል ሱስ ይወድቃሉ። ስኪዞፈሪንያ እና የዕፅ ሱስን አንድ ላይ የሚያክም የሕክምና ፕሮግራም መኖሩ በጣም ጠቃሚ ነው። ምክንያቱም አደንዛዥ እጽ መጠቀም የስኪዞፈሪንያ ሕክምናን ሊያስተጓጉል ይችላል።

ለስኪዞፈሪንያ እርዳታ እንዴት ማግኘት እችላለሁ?

እርዳታ የት እንደሚያገኙ እርግጠኛ ካልሆኑ፣ መጀመርያ ሀኪምዎን ያማክሩ። ሐኪምዎ ስኪዞፈሪንያ የማከም ልምድ ወዳለው እንደ ሳይካትሪስት ወይም ሳይኮሎጂስት ላሉ ብቁ የአእምሮ ጤና ባለሙያ ሊልክዎ ይችላል። ቅድመ ዝግጅት ለማድረግ የሚረዱ አንዳንድ ምርጥ ምክሮችን እዚህ ያግኙ።

የአደንዛዥ እጽ እና የአእምሮ ጤና አገልግሎት አስተዳደር ድረገጽን በመጠቀም በአካባቢዎ ያሉ የአእምሮ ጤና አገልግሎት ማእከላትን በቀላሉ ማግኘት ይችላሉ። ይህ ድረ ገጽ ገና በጅምር ያለ ከባድ የየአእምሮ በሽታ ህክምና ማእከላትንም ይጠቁማል።

የስነልቦና ችግር ያለበትን ሰው እንዴት መርዳት እንደሚቻል ማወቅ አስቸጋሪ ሊሆን ይችላል።

ማድረግ የምትችላቸው አንዳንድ ነገሮች እነሆ፡-

  • ህክምና እንዲያገኙ መርዳት እና በህክምናው እንዲቆዩ ማበረታታት።
  • የእነሱ እምነት ወይም ቅዠት ለእነርሱ በጣም እውነት እንደሚመስሉ ልብ ልንል ይገባል።
  • ህመመተኛቹ አደገኛ ወይም ተገቢ ያልሆነ ባህሪ ሲያሳያ አይታገሱ፤ ነገር ግን አክባሪ፣ ደጋፊ እና ደግ ይሁኑላቸው።
  • የድጋፍ ቡድኖችን እና የቤተሰብ ትምህርት ፕሮግራሞችን ይፈልጉ፣ ለምሳሌ ብሔራዊ የአእምሮ ሕመም መከላል ጥምረት  የሚያቀርባቸውን አይነት።

https://www.nimh.nih.gov/health/topics/schizophrenia

ስለ ስኪዞፈሪንያ የበለጠ ማወቅ የምችለው የት ነው?

ነፃ ብሮሹሮች እና ሊጋሩ የሚችሉ ሀብቶች

  • ስኪዞፈሪንያ፦ ይህ የስኪዞፈሪንያ ብሮሹር ስለ ምልክቶቹ፣ የህክምና አማራጮች እና እርዳታ ስለማግኘት መሰረታዊ መረጃዎችን ይሰጣል። በስፔንኛም ይገኛል።
  • ሳይኮሲስን መረዳት፡ ይህ የእውነታ በራሪ ወረቀት ስለ ምልክቶቹ፣ የህክምና አማራጮች እና እርዳታ ስለማግኛ መንገዶዲ መሰረታዊ መረጃዎችን ይሰጣል። በስፔንኛም ይገኛል።
  • ስለ ስኪዞፍረኒያ ሊጋሩ የሚችሉ ዲጂታል መረጃዎች፦ እነዚህ ዲጂታል ግብዓቶች፣ ግራፊክስ እና መልዕክቶችን ጨምሮ፣ ስለ ስኪዞፈሪንያ መረጃ ለማሰራጨት እና ማህበረሰቡን ስለ ስኪዞፈሪንያ ግንዛቤ እና ትምህርት ለማስጨበጥ ይረዳሉ።

ምርምር እና ስታቲስቲክስ

  • Accelerating Medicines Partnership Program Schizophrenia (AMP SCZ): ይህ ፕሮግራም ዓላማው በስኪዞፈሪንያ የመያዝ አደጋ ላለባቸው ሰዎች ውጤታማ ሕክምናዎችን ማቅረብ ነው። ስለ ፕሮግራሙ ተጨማሪ መረጃ በAMP SCZ ድህረ ገጽ ላይም ይገኛል።
  • Early Psychosis Intervention Network: ይህ ሰፊ የምርምር ማህበር  የሳይኮሲስ ችግር መታየት ለጀመረባቸው ታማሚዎች ልዩ የህክምና አገልግሎቶችን ውጤታማ በሆነ መንገድ ለማቅረብ ምቹ የሆኑ ሞዴሎችን የሚያጠና ነው።
  • የጆርናል አርቲክሎች፡ ይህ ድረ-ገጽ የብሔራዊ የሕክምና ቤተ መፃህፍት ግብአቶችን ዋቢ ያደረጉ መረጃዎችን ያቀርባል።
  • Psychotic Disorders Research Program: ይህ ፕሮግራም የስኪዞፈሪንያ ስፔክትረም ዲስኦርደር እና ሌሎች የስነልቦና በሽታዎች አመጣጥ፣ አጀማመር፣ ሂደት እና ውጤት ላይ ያተኮሩ ምርምሮችን ይደግፋል።
  • Risk and Early Onset of Psychosis Spectrum Disorders Program: ይህ ፕሮግራም በልጅነት እና በጉርምስና ዕድሜ የሚከሰቱ የስነ ልቦና እና የአስተሳሰብ መዛባት ችግሮል ላይ የሚሰሩ ጥናቶችን ይደግፋል።
  • Recovery After an Initial Schizophrenia Episode: ይህ የምርምር ፕሮግራም ሳይኮሲስ መታየት እየጀመረ ላለባቸው ታካሚዎች ስለሚሰጠው የተቀናጀ ልዩ ህክምና የሚያጠና ለሁለት የተከፈለ ጥናቶችን የያዘ ነው።
  • ስታትስቲክስ፡ ስኪዞፈሪንያ፡ ይህ ድረ-ገጽ በዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ ባሉ ሰዎች  የስኪዞፈሪንያ ስርጭት ምን እንደሚመስል እና ስለ ሕክምናው በአሁኑ ጊዜ ያለውን ስታቲስቲክስ ያቀርባል።

መልቲሚዲያ

  • ስለ ስኪዞፍሬኒያ የNIMH ባለሙያዎች ውይይት፡ ከዚህ ድረ ገጽ ስለ ስኪዞፍሬኒያ ምልክቶች እና ስለ መንስኤዎቹ፣ ስለ ህክምናዎቹ እና ስለ ቅርብ ጊዜ የምርምር ውጤቶችን ያገኛሉ።

ለመጨረሻ ጊዜ የተገመገመ ፡ ሜይ 2023

This post is also available in: English (እንግሊዝኛ)

Index