Emergency? Call 911 በማንኛውም የአደጋ ጊዜ ወደ 911 ይደውሉ Feeling hopeless? Call or Text 988 የተስፋ መቁረጥ ስሜት ከተሰማዎት ወደ 988 ይደውሉ 911 and 988 work in the US & Canada. On a US 988 call, say “Amharic” to ask for a free interpreter. 911 እና 988 በአሜሪካና በካናዳ ይሠራሉ። በአሜሪካ ወደ 988 ሲደውሉ “Amharic” ብለው ነጻ አስተርጓሚ ይጠይቁ። ከአሜሪካና ካናዳ ውጭ ነዎት? የሌሎች አገሮች የእርዳታ መስመሮች →
የወይራ ቅጠሎችና ሚዛናዊ የጂኦሜትሪ ንድፎች በብራና ቀለም መደብ ላይ

መድሃኒቶች የአእምሮ መዛባትን እና ህመሞችን በማከም ረገድ ሚና ሊጫወቱ ይችላሉ፤ እናም ብዙ ጊዜ ከሳይኮቴራፒ፣ ከአንጎል ማነቃቂያ ቴራፒ እና መሰል የሕክምና ዘዴዎች ጋር በማጣመር ጥቅም ላይ ይውላሉ። መድሃኒቶች በተለያዩ ሰዎች ላይ የተለያየ ውጤት ሊኖራቸው ይችላሉ፤ ስለዚህ በጣም ውጤታማ እና አነስተኛ የጎንዮሽ ጉዳት ያለውን መድሃኒት ለማግኘት ብዙ ጊዜ መሞከር ሊያስፈልግ ይችላል። ሰዎች ፍላጎቶቻቸውን እና የሕክምና ሁኔታቸውን የሚያሟላ የሕክምና ዕቅድ ለማዘጋጀት ከጤና እንክብካቤ አቅራቢ ወይም ከአእምሮ ጤና ባለሙያ ጋር አብረው መሥራት ያስፈልጋቸዋል።

ስለ መድሃኒቶች የሚወጡ መረጃዎች በየጊዜው ይዘምናሉ። ቅርብ ጊዜ ስለ ወጡ ማስጠንቀቂያዎች፣ ስለ መድኃኒት መመሪያዎች እና አዲስ በሳይንስ ተረጋግጠው ተቀባይነት ስላገኙ መድኃኒቶች መረጃ ለማግኘት የ U.S የምግብ እና የመድኃኒት አስተዳደር (FDA) የመድኃኒት መመሪያ ድረ-ገጽን ይጎብኙ። እንዲሁም The MedlinePlus Drugs፣ Herbs እና Supplements የተሰኙ ድረ-ገጽም ስለ መድሐኒቶች፣ ስለጎንዮሽ ጉዳቶች፣ እና ከFDA ስለሚወጡ ማስጠንቀቂያዎች መረጃዎችን ይሰጣሉ።

ይህ ድረ-ገፅ ስለ አእምሮ ጤና መድኃኒቶች መሰረታዊ መረጃዎችን ይሰጣል። ነገር ግን ስለ ሁሉም መድሃኒቶች መረጃ ስለማይሰጥ የህክምና ውሳኔዎችን ለመወሰን እንደ መመሪያ ልንጠቀመው አይገባም።

ተዛማጅ ርዕሶች