ልዩ ቡድኖች - ህጻናት እና ታዳጊዎች
የአእምሮ መታወኮችን ለማከም የሚያገለግሉ ብዙ መድኃኒቶች ለሕፃናትና ለታዳጊዎች ደህንነታቸው የተጠበቀና ውጤታማ ናቸው። ይሁን እንጂ ሕፃናት ከአዋቂዎች የተለየ ምላሽና የጎንዮሽ ጉዳት ሊያጋጥማቸው እንደሚችል፣ እንዲሁም አንዳንድ መድኃኒቶች በወጣቶች ላይ ሊከሰቱ ስለሚችሉ የጎንዮሽ ጉዳቶች የFDA ማስጠንቀቂያ እንዳላቸው ማወቅ አስፈላጊ ነው።
በአንዳንድ ሁኔታዎች የጤና ባለሙያ በFDA የተፈቀደን መድኃኒት፣ ለዚያ የሕፃኑ የአእምሮ መታወክ ወይም ከተወሰነ ዕድሜ በታች ላሉ ሰዎች ባይፈቀድም፣ የሕፃኑን ምልክቶች ለማከም “ከተፈቀደለት ዓላማ ውጭ” (off-label) ሊያዝዝ ይችላል። በሕፃናት የአእምሮ መታወኮች ላይ የተደረገው ምርምር በአዋቂዎች ላይ ከተደረገው ያነሰ ቢሆንም፣ መድኃኒቶች ሕፃናትን ሊረዱ እንደሚችሉ የሚያሳዩ አንዳንድ መረጃዎች አሉ። መድኃኒትን “ከተፈቀደለት ዓላማ ውጭ” የሚወስዱ ሕፃናትንና ታዳጊዎችን በቅርበት መከታተል አስፈላጊ ነው።
የሕፃኑ የጤና ባለሙያ መጀመሪያ እንደ ሳይኮቴራፒ ያሉ ከመድኃኒት ውጪ የሆኑ ሕክምናዎችን እንዲሞከሩ ሊመክር፣ ካስፈለገም በኋላ መድኃኒት ሊጨምር ይችላል። በሌሎች ሁኔታዎች ደግሞ የጤና ባለሙያው ከመድኃኒት ውጪ የሆነ ሕክምናን ከመድኃኒት ጋር አጣምሮ ሊመክር ይችላል። የብሔራዊ የአእምሮ ጤና ተቋም (NIMH) Children and Mental Health: Is This Just a Stage? የተሰኘው የመረጃ ወረቀት ለሕፃናትና ለታዳጊዎች ስለተለመዱ የሕክምና አማራጮች ተጨማሪ መረጃ ይሰጣል።