ተጓዳኝ በሽታዎች
ተጓዳኝ በሽታ ማለት ከሌላ የጤና ችግር ጋር አብሮ የሚከሰት የጤና ችግር ነው። ለረጅም ጊዜ የሚቆዩ የአካል ሕመሞች እና የአእምሮ ጤና ችግሮች ብዙ ጊዜ እርስ በርስ ይነካካሉ፦ ሥር ከሰደደ ሕመም ጋር መኖር ለድባቴ ወይም ለጭንቀት የመጋለጥ ዕድልን ሊጨምር ይችላል፤ የአእምሮ ጤና ችግር ደግሞ የአካል ጤናን መንከባከብ ከባድ ሊያደርገው ይችላል። ሁለቱንም በአንድነት ማከም የተሻለ ጤና ያስገኛል። ከታች ያለው መመሪያ ስለ ኤች አይ ቪ/ኤድስ እና የአእምሮ ጤና ያብራራል።