Emergency? Call 911 በማንኛውም የአደጋ ጊዜ ወደ 911 ይደውሉ Feeling hopeless? Call or Text 988 የተስፋ መቁረጥ ስሜት ከተሰማዎት ወደ 988 ይደውሉ 911 and 988 work in the US & Canada. On a US 988 call, say “Amharic” to ask for a free interpreter. 911 እና 988 በአሜሪካና በካናዳ ይሠራሉ። በአሜሪካ ወደ 988 ሲደውሉ “Amharic” ብለው ነጻ አስተርጓሚ ይጠይቁ። ከአሜሪካና ካናዳ ውጭ ነዎት? የሌሎች አገሮች የእርዳታ መስመሮች →

የድባቴ ቅድመ ምርመራ ለምን ይጠቅማል?

የማለዳ ፀሐይ ጭጋጉን ስትገልጥ በአረንጓዴ ኮረብቶች ላይ የፈኩ ወርቃማ የአደይ አበቦች

የእንቅልፍ ችግር፣ የማይለቅ ሐዘንና ቀድሞ ያስደስቱዎት በነበሩ ነገሮች ላይ ፍላጎት ማጣት ከድባቴ ምልክቶች መካከል ናቸው። ድባቴ የተለመደ ሕመም ነው፤ ይታከማልም።

የድባቴ ቅድመ ምርመራ የሚጠቅምዎባቸው መንገዶች፦

  1. 1. ችግሩን ቀድሞ ማወቅ

    ሌሎች ምርመራዎች የአካል ጤናዎን እንደሚፈትሹ ሁሉ የድባቴ ቅድመ ምርመራም የአእምሮ ጤናዎን ይፈትሻል። የድባቴ ምልክቶች ከመባባሳቸው በፊት ቀድመው እንዲታወቁ ያስችላል።

  2. 2. ሕክምናን ቶሎ መጀመር

    ቅድመ ምርመራው የድባቴ ምልክቶችን ካሳየ ባለሙያ ቶሎ ማየትና ሕክምና ቶሎ መጀመር ይችላሉ።

  3. 3. በዕለት ተዕለት ኑሮ ላይ የሚደርሰውን ጉዳት መቀነስ

    ድባቴ ሳይታከም ከቀረ በዕለት ተዕለት ኑሮዎ፣ በግንኙነቶችዎና በአጠቃላይ ጤናዎ ላይ ከፍተኛ ጉዳት ሊያደርስ ይችላል። ቀድሞ መያዙ ይህን ጉዳት ሊቀንስ ይችላል።

  4. 4. ስለ ጉዳዩ መነጋገርን ማቅለል

    ቅድመ ምርመራ የሐኪም ጉብኝት መደበኛ አካል ሲሆን፣ የአእምሮ ጤና ከሐኪም ጋር በቀላሉ የሚነሳ ርዕስ ይሆናል። ይህም መገለልን ሊቀንስና ድባቴ ያለባቸው ሰዎች እርዳታ መጠየቅ እንዲቀልላቸው ሊያደርግ ይችላል።

  5. 5. የመደበኛ ሕክምና አካል

    የደም ግፊትዎን ወይም ኮሌስትሮልዎን እንደሚያስለኩ ሁሉ የድባቴ ቅድመ ምርመራም የመደበኛ የጤና ክትትልዎ አካል ሊሆን ይችላል።

ቅድመ ምርመራ በእርስዎ ላይ የሚሰጥ ፍርድ አይደለም። ለአእምሮ ጤናዎ ልክ እንደ አካል ጤናዎ ትኩረት የሚሰጡበት መንገድ ነው።

ከላይ ከተጠቀሱት ምልክቶች አንዱም ካለብዎ ስለ ድባቴ ቅድመ ምርመራ ሐኪምዎን ይጠይቁ።