ለአእምሮ ጤና አራት የዕለት ተዕለት ልማዶች
የአእምሮ ጤናን መንከባከብ የዕለት ተዕለት ጫናዎችን ለመቋቋም ያግዛል። በዚህ ሳምንት ሊጀምሯቸው የሚችሉ አራት ልማዶች እነሆ፦
ለአእምሮ ጤና 4 የዕለት ተዕለት ልማዶች
-
01 የዕለት የጤና እቅድ ያዘጋጁ
ለአእምሮና ለአካል ጤናዎ በየቀኑ ትንሽ ጊዜ ይመድቡ፦ ለተመስጦ፣ ለማስታወሻ፣ ከቤት ውጭ ለመሆን ወይም ለሚወዱት የትርፍ ጊዜ ተግባር።
-
02 ስሜቶችን ይግለጹ
ከባድ ስሜቶችን በውስጥዎ ከመያዝ ይልቅ ለሚያምኑት ጓደኛ፣ ዘመድ ወይም አማካሪ ይንገሩ።
-
03 ጭንቀትዎን ይቆጣጠሩ
መደበኛ የአካል እንቅስቃሴና በዝግታ መተንፈስን ይጠቀሙ፤ ሥራ ሲበዛብዎ አዲስ ኃላፊነት ላለመቀበል ‹‹አይ›› ይበሉ።
-
04 ግንኙነትና ደግነት
ትናንሽ የደግነት ተግባራት የሌሎችንም የራስዎንም ስሜት ሊያሻሽሉ ይችላሉ።
1. ለአእምሮ ጤናዎ የዕለት ተግባር ያዘጋጁ፦ ለአካል እንቅስቃሴ ጊዜ እንደሚመድቡ ሁሉ ለአእምሮ ጤናዎም ጊዜ ይመድቡ። በየቀኑ የሚያደርጓቸውን ጥቂት ነገሮች ይምረጡ፤ ለምሳሌ ማሰላሰል (ሜዲቴሽን)፣ ሐሳብዎንና ስሜትዎን በማስታወሻ መጻፍ፣ ከቤት ውጭ ጊዜ ማሳለፍ ወይም የሚወዱት የትርፍ ጊዜ ተግባር። ሥራ በበዛበት ቀንም ይህን ልማድ አያቋርጡ።
2. ስለ ስሜትዎ ይናገሩ፦ ስሜትን አፍኖ መያዝ ውጥረትን ሊጨምርና የአእምሮ ጤናን ሊጎዳ ይችላል። እንደ ጓደኛ፣ ቤተሰብ ወይም ቴራፒስት ላሉ ለሚያምኗቸው ሰዎች ይንገሩ። በማስታወሻ መጻፍም ሐሳብዎንና ስሜትዎን ለመለየትና ለመረዳት ይረዳል። ስሜትዎን አምኖ መቀበልና መናገር ድክመት አይደለም።
3. ውጥረትን ቀድመው ይቆጣጠሩ፦ ጫናዎች ሳይፈቱ ሲከማቹ ውጥረት ይጨምራል፤ ስለዚህ ከመከማቸታቸው በፊት እርምጃ ይውሰዱ። ከፈጠን ያለ የእግር ጉዞ እስከ ጠንከር ያለ ስፖርት ድረስ መደበኛ የአካል እንቅስቃሴ ውጥረትን ለመቀነስ ይረዳል። ጥልቅ ትንፋሽ ወይም ማሰላሰል ውጥረት በተሰማዎ ጊዜ ለመረጋጋት ይረዳል። ቅድሚያ የሚሰጡትን ይለዩ፤ ገደብም ያስቀምጡ። ሥራ ሲበዛብዎ ያለብዎትን ኃላፊነቶች ራስዎን ሳያደክሙ ለመወጣት በትሕትና ‹‹አይ›› ይበሉ።
4. ደግ ይሁኑ፤ ከሰዎች ጋር ይገናኙ፦ ደግነት ሰዎች እርስ በርስ እንዲቀራረቡ ይረዳል። ለማያውቁት ሰው ፈገግ ይበሉ፣ ከልብ የሆነ አድናቆት ይስጡ ወይም ለሌላው በሩን ከፍተው ይያዙ። እንዲህ ያሉ ትናንሽ ተግባራት የራስዎንም ስሜት ሊያሻሽሉ ይችላሉ። ለሌሎች ደህንነት ትኩረት መስጠት የራስዎንም ደህንነት ይጠቅማል።