Skip to content
Home » መድሃኒቶች » ልዩ ቡድኖች – እድሜያቸው የገፋ አዋቂዎች

ልዩ ቡድኖች – እድሜያቸው የገፋ አዋቂዎች

ከ 65 ዓመት በላይ የሆኑ ሰዎች፣ በተለይ ብዙ የተለያዩ መድሃኒቶችን የሚወስዱ ከሆነ፣ መድኃኒት ሲወስዱ የበለጠ ጥንቃቄ ማድረግ አለባቸው። በዕድሜ የገፉ ሰዎች የመድኃኒት ተጠቃሚ የመሆኑ እድላቸው ከፍ ያለ ሲሆን ብዙውን ጊዜ አመድኃት ጋር ለተያያዙ ችግሮች የበለጠ ተጋላጭ ናቸው። የጤናማ አረጋውያን ሰውነትም ለመድኃኒት ከወጣቶች በተለየ መልኩ ምላሽ ይሰጣል። ምክንያቱም በአረጋውያን ሰውነት መድሃኒት በዝግታ ሠርቶ በዝግታ ከሰውነት ይወገዳል።

መድሃኒት ከመጀመራቸው በፊት፣ አረጋውያን እና ቤተሰባቸው መድሃኒቱ በአረጋዊው አካል እና የአእምሮ ስራ ላይ ስለሚኖረው ተጽእኖ ከጤና ባለሙያዎች ጋር መነጋገር አለባቸው። የጤና እንክብካቤ አቅራቢው ከታካሚው ጋር በመሆን የሕክምና እቅዱን ለመከተል የሚረዱ ስልቶችን መቅረጽ አለበት። ይህም አረጋውያን ትክክለኛውን የመድሃኒት መጠን በትክክለኛው ጊዜ እንዲወስዱ ይረዳል።

National institute on agings የተሰኘ ተቋም ያዘጋጀው ቡክሌት ለአረጋውያን ጤናማ የመድሐኒታት አጠቃቀምን ለማረጋገጥ የሚረዱ ምክሮችን ይሰጣል። ‍️

This post is also available in: English (እንግሊዝኛ)