Skip to content
Home » መድሃኒቶች » ልዩ ቡድኖች – ህጻናት እና ታዳጊዎች

ልዩ ቡድኖች – ህጻናት እና ታዳጊዎች

የአእምሮ ሕመሞችን ለማከም የሚያገለግሉ ብዙ መድኃኒቶች ለህጻናት እና ታዳጊዎች ውጤታማ እና ደህንነታቸውም የተጠበቀ ናቸው። ነገር ግን ልጆች ከአዋቂዎች በበለጠ የጎንዮሽ ጉዳቶች እና ምልክቶች ሊያጋጥማቸው ይችላል። እናም አንዳንድ መድሃኒቶች በተለይ ታዳጊዎች ላይ የጎንዮሽ ጉዳቶች እንዳላቸው FDA ያስጠነቅቃል።

በአንዳንድ ሁኔታዎች፣ የጤና ባለሙያዎች ለህጻኑ እድሜ ያልተፈቀደ መድሐኒት ወይም ለህጻኑ እድሜ ያልተፈቀደ ዶዝ ሊያዝዙ ይችላሉ፤ ምንም እንኳ መድሐኒቱ በFDA እውቅና ያገኘ ቢሆንም። በህጻናት የአእምሮ ሕመም ላይ የተደረገ ጥናት በአዋቂዎች የአእምሮ ህመም ላይ ከተደረገው ያነሰ ቢሆንም፣ መድኃኒቶች ህጻናትን ለማከም ጠቃሚ እንደሆኑ የሚያሳዩ አንዳንድ መረጃዎች አሉ። በልዩ ምክንያት በFDA እና መሠል ተቆጣጣሪ ድርጅቶች በኩል ከወጡ የመድኃኒት አወሳሰድ መመርያዎች በወጣ መንገድ መድሐኒቶች የሚወስዱ ህጻናት የህክምና ባልሙያዎች ክትትል ያስፈልጋቸዋል።

ሀኪሞች ህጻኑ በመጀመሪያ እንደ ሳይኮቴራፒ ያሉ ከመድሐኒት ወጪ የሆኑ ሕክምናዎችን እንዲሞክር ካደረጉ በኋላ ነው በመጨረሻ ወደ መድሐኒት መምጣት ያለባቸው። በአንዳንድ ሁኔታዎች ደግሞ ሐኪሞች ከመድሃኒት ውጪ የሆኑ ህክምናዎችን ከመድሐኒት ጋር በማጣመር ተግባራዊ ሊያደርጉ ይችላሉ። The National Institute of Mental Health (NIMH) fact sheet Children and Mental Health: Is This Just a Stage? ይህ ገጽም ለህጻናት እና ለወጣቶች የተለመዱ የሕክምና አማራጮችን በተመለከተ ተጨማሪ መረጃ ይሰጣል።

This post is also available in: English (እንግሊዝኛ)