Skip to content
Home » መድሃኒቶች » ልዩ ቡድኖች – ነፍሰ ጡሮች

ልዩ ቡድኖች – ነፍሰ ጡሮች

ሳይንቲስቶች በእርግዝና ወቅት የአእምሮ ጤና መድሃኒት አጠቃቀምን በተመለከተ ምርምራቸውን ቀጥለዋል። በእርግዝና ወቅት መድሃኒት ከመውሰድ ጋር የተያያዙ አደጋዎች በመድሃኒት ዓይነት እና በእርግዝናው ደረጃ ይወሰናሉ። በእርግዝና ወቅት የሚወሰድ ከደህንነት ስጋት  ሙሉ በሙሉ ነጻ የሆነ አንድም መድሃኒት ባይኖርም፣ ያልታከመ የአእምሮ ህመምም በነፍሰ ጡሯ እና በፅንሱ ላይ ትልቅ አደጋ ሊያስከትል ይችላል።

ነፍሰ ጡሯ እና የጤና አገልግሎት አቅራቢው የግል ፍላጎቶችን እና ሁኔታዎችን ያገናዘበ ግላዊ የህክምና እቅድ ለማዘጋጀት አብረው መስራት አለባቸው። ከሁሉም የሕክምና አማራጮች ጋር የተያያዙ ጥቅሞችን እና አደጋዎችን በሚገባ ማመዛዘን በጣም አስፈላጊ ነው፤ ህክምናው ሳይኮቴራፒ፣ መድኃኒት፣ የአንጎል ማነቃቂያ ሕክምና ወይም የእነዚህ ጥምረት ሊሆን ይችላል። የጤና አገልግሎት አቅራቢዎች የነፍሰጡሯን አካላዊ እና አእምሯዊ ጤንነት በእርግዝና ወቅት እና ከወሊድ በኋላ በቅርበት መከታተል አለባቸው። በተለይ የወሊድ ወይም የድህረ ወሊድ ድብርት ምልክቶች ላይ ትኩረት ሊሰጥ ይገባል።

ቤንዞዲያዜፒንስ፣ ሙድ ስታብላይዘር፣ አንቲሳይኮቲክ እና መሰለ መድሐኒቶች በእርግዝና ወቅት ሲወሰዱ የሚወለደው ህጻን ላይ ቋሚ የጤና ችግር ሊያስከትሉ ይችላሉ፤ ነገር ግን አደጋው በጣም የተለያየ እና በመድሃኒቱ አይነት የሚወሰን ነው።

ፀረ-ድባቴ መድሐኒቶች በአጠቃላይ፣ በተለይም SSRI መድኃኒቶች፣ በእርግዝና ወቅት ብዙም አደጋ እንደማያስከትሉ ይቆጠራሉ። ፀረ-ድባቴ መድሐኒቶች ፕላሴንታን አልፈው ወደ ፅንሱ ሊደርሱ ይችላሉ፤ ነገር ግን የሚወለደው ህጻን ላይ ቋሚ የጤና ችግር እና ሌሎች ችግሮችን የማስከተል ስጋቱ በጣም ዝቅተኛ ነው። አንዳንድ ጥናቶች Third-trimester SSRI በሚባለው ጎራ የሚመደቡ መድሐኒቶች በሚወለደው ህጻን ላይ የአተነፋፈስ ችግር እና መሠል ችግሮች ሊያስከትሉ እንደሚችሉ ፍንጭ ይሰጣሉ። ይሁን እንጂ FDA መድኃኒቶቹ የተጠቀሱትን ችግሮች ስለማስከተላቸው በቂ ማስረጃ አላገኘም፤ በመሆኑም FDA በእርግዝና ወቅት ድባቴን የነፍሰ ጡሯን ፍላጎት እና ሁኔታ ባገናዘበ ሁኔታ በጸረድባቴ መድሐኒቶች ማከም ችግር እንደሌለው ይገልጻል።

ስለ መድሃኒቶች እና እርግዝና ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት የFDA ድህረ ገጽን ይጎብኙ።

This post is also available in: English (እንግሊዝኛ)