የጤና እንክብካቤ አቅራቢዎች ADHDን እና ናርኮሌፕሲን ሲያክሙ አነቃቂ መድሃኒቶችን ሊያዝዙ ይችላሉ። አነቃቂ መድኃኒቶች ንቃትን፣ ትኩረትን እና ጉልበትን ይጨምራሉ። በተጨማሪም የደም ግፊትን፣ የልብ ምትን እና የአተነፋፈስ መጠንን ከፍ ሊያደርጉ ይችላሉ።
ተጠቃሚው የህምና ምርመራ ማድረግ ሳይኖርበት፣ በሐኪም የሚታዘዙ አነቃቂ መድኃኒቶች ለአብዛኛው ሰው ንቃትን እና ትኩረትን ያሻሽላሉ። እነኚያ መድሃኒቶች ከፍተኛ የትኩረት ችግር ላለባቸው ሰዎች የእለት ተእለት ተግባራቸው ላይ ትልቅ አዎንታዊ ለውጥ ሊያመጡ ይችላሉ፤ ለምሳሌ ADHD ባለባቸው ሰዎች። ADHD ምክንያት የሚፈጠር ከመጠን በላይ የመፍጠን ችግር ብዙ ጊዜ ህጻናት ወደ ጉርምስና ዕድሜ ሲደርሱ የሚጠፋ ቢሆንም፣ ትኩረት ማድረግ ያለመቻል ችግር ግን በጉልማሳነት እድሜም ሊቀጥል ይችላል። እንዲህ ባሉ ሁኔታዎች፣ አነቃቂ መድሃኒቶች ADHD ላለባቸው አዋቂዎች፣ እንዲሁም ADHD ላለባቸው ህጻናት እና ጎረምሶች ጠቃሚ ሊሆኑ ይችላሉ።
አነቃቂ መድሃኒቶች በጤና እንክብካቤ አቅራቢዎች ክትትል ስር እና በመመርያ መሠረት ሲወሰዱ የደህንነት ስጋታቸው በከፍተኛ ደረጃ ይቀንሳል። መድሐኒቶቹን የሚወስዱ አንዳንድ ህጻነት ትንሽ ለየት ያለ ስሜት ሊሰማቸው እና አንዳንዴም “አስቂኝ” ምልክቶች ሊታይባቸው ይችላል። አብዛኛዎቹ የአነቃቂ መድሃኒቶች የጎንዮሽ ጉዳቶች ተራ እና ዶዝ በማስተካከል የሚጠፉ ናቸው።
አንዳንድ ወላጆች ልጆቻቸው አነቃቂ መድሃኒት መጠቀማቸው ልጆቹን መድሐኒቱን አላግባብ ወደ መጠቀም ወይም መድኃኒቲ ላይ ጥገኛ ወደ መሆን እንዳያመራቸው ይሰጋሉ። ነገር ግን መድሃኒቶቹ በታዘዘው መሰረት ጥቅም ላይ ሲውሉ ይህ የማይከሰት መሆኑን መረጃዎች ያሳያሉ። የእንቅልፍ መዛባት፣ የእድገት መዘግየት እና ሌሎች ከአነቃቂ መድኃኒትቶች ጋር የተ
ያያዙ ችግሮችም ከጤና ባለሙያው ጋር በመተባበር በአስተማማኝ ሁኔታ የሚቀረፉ ናቸው።
This post is also available in:
English (እንግሊዝኛ)
