Skip to content
Home » መድሃኒቶች » አንቲሳይኮቲክስ

አንቲሳይኮቲክስ

አንቲሳይኮቲክ መድሐኒቶች በተለምዶ ሳይኮሲስ የሚባለውን የአእምሮ ችግር ለማከም ያገለግላሉ፣ ሳይኮሲስ ውስጥ ያሉ ሰዎች ለብቻ የማውራት እና መሠል ከእውነታ የማይገኙ ተግባራትን ያደርጋሉ። ሳይኮሲስ ውስጥ ያሉ ሰዎች ብዙ ጊዜ Delusion (የሐሰት እምነቶች) ወይም Hallucinations (ሌሎች የማያዩትን ወይም የማይሰሙትን ነገር መስማት ወይም ማየት) ያጋጥማቸዋል። ሳይኮሲስ ከአደንዛዥ ዕፅ አጠቃቀም ወይም ስኪዞፈሪንያ፣ ባይፖላር ዲስኦርደር፣ ከፍተኛ ድባቴ (“ሳይኮቲክ ዲፕሬሽን” በመባልም ይታወቃል) እና መሠል የአእምሮ ችግሮች ጋር ሊያያዝ ይችላል።

የአእምሮ ጤና ሐኪሞች Delirium፣ Dementia እና ሌሎች የአእምሮ እክሎችን ለማከም አንቲሳይኮሲስ መድሐኒቶችን ከሌሎች መድሃኒቶች ጋር በማጣመር ሊጠቀሙ ይችላሉ። አንቲሳይኮሲስ ሕክምና ለአረጋውያን ሲሰጥ ተጨማሪ ጥንቃቄ እና እንክብካቤ ያስፈልገዋል። FDA ሁሉም አንቲሳይኮሲስ መድሐኒቶች እላያቸው ላይ አንቲሳይኮሲስ መድሐኒቶች Dementia ያለባቸው አዛውንቶች ላይ ከሚከሰት እያደገ ከመጣ የስትሮክ እና ሞት መጠን ጋር ትይይዝ እንዳላቸው የሚያስገነዝብ ማስጠንቀቂያ እንዲጻፍ ያስገድዳል።

የቆዩ፣ ወይም የመጀመሪያ ትውልድ አንቲሳይኮቲክ መድሐኒቶች አንዳንድ ጊዜ “Typical” አንቲሳይኮቲክስ ወይም “Neuroleptics” በመባል ይታወቃሉ። Typical አንቲሳይኮቲክ መድሐኒቶችን ለረጅም ጊዜ መጠቀም Tardive Dyskinesia(TD) የሚባለውን ከቁጥጥር ውጪ የሆነ የጡንቻ እንቅስቃሴ እክልን ሊያስከትል ይችላል። TD በሽታ የአደገኝነቱ መጠን ከቀላል እስከ ከባድ ሊደርስ ይችላል። TD እንዳለባቸው የሚያስቡ ሰዎች መድሃኒቶቻቸውን ከማቆማቸው በፊት ከጤና ባለሙያቸው ጋር መማከር አለባቸው።

አዲስ፣ ወይም የሁለተኛ-ትውልድ አንቲሳይኮቲክ መድሐኒቶች አንዳንድ ጊዜ “Atypical”  መድኃኒት ይባላሉ። ከ Typical  መድሃኒቶች ጋር ሲነፃፀሩ፣ Typical መድሐኒቶች ሰፋ ያሉ የሕመም ምልክቶችን ለማከም ጥቅም ላይ ሊውሉ ይችላሉ። ለምሳሌ እነዚያ መድሃኒቶች አንዳንድ ጊዜ ለፀረ-ድባቴ መድሃኒት ምላሽ ያልሰጡ የድባቴ በሽታዎችን እና ባይፖላር ዲፕሬሽንን ለማከም ያገለግላሉ። ሀኪሞች Typical አንቲሳይኮቲክ መድሃኒት የሚወስዱ ሰዎችን በመደበኛነት የክብደት፣ የግሉኮስ መጠን እና የስብ መጠንናቸውን እንዲለኩ ሊያስታውሷቸው ይገባል።

ከመድሐኒቶቹ ጋር የተያያዙ ታካሚዎች ላይ የሚታዩ የብስጭት፣ የቅዠት እና መሰል ምልክቶች ብዙ ጊዜ አንቲሳይኮቲክ መድሐኒቶችን በጀመሩ በቀናት ውስጥ ይጠፋሉ። Delusionsን የመሳሰሉ ሌሎች ምልክቶች ደግሞ ብዙ ጊዜ ታካሚው መድሐኒቶቹን በጀመረ በጥቂት ሳምንታት ቆይታ ይጠፋሉ። ሆኖም ሰዎች የአንቲሳይኮሲስ መድኃኒቶች የተሟላ ተጽእኖ እስከ 6 ሳምንታት ድረስ ላያሰማቸው ይችላል።

የታካሚው ጤና በተለመዱት የአንቲሳይኮቲክ መድሃኒቶች መሻሻል ካላሳየ Clozapine የተባለውን Atypical አንቲሳይኮቲክ መድሃኒት ሊታዘዝለት ይችላል። Clozapine የተሰኘውን መድሐኒት የሚወስዱ ሰዎች ከ1% እስከ 2% በመቶ የሚሆኑ ሰዎች ላይ የሚከሰተውን አደገኛ የሆነ የጎንዮሽ ጉዳት ለመፈተሽ መደበኛ የደም ምርመራ ማድረግ አለባቸው

This post is also available in: English (እንግሊዝኛ)