Skip to content
Home » መድሃኒቶች » የስሜት ማረጋጊያ መድሐኒቶች

የስሜት ማረጋጊያ መድሐኒቶች

የስሜት ማረጋጊያ መድሐኒቶች የስሜት መለዋወጥን ለማመጣጠን እና በተለምዶ ባይፖላር ዲስኦርደር በሚሰኝ እና በሌሎች የአእምሮ ጤና እክሎች የሚከሰቱ የስሜት መረበሾችን ለማረጋጋት ያገለግላሉ። ሀኪሞች ድባቴን ለማከም ከሌሎች መድሃኒቶች ጋር ቀላቅለው የስሜት ማረጋጊያዎችን ሊሰጡ ይችላሉ። ሊቲየም የተሰኘው መድሐኒት ባይፖላር ዲስኦርደር ባለባቸው ሰዎች ላይ የሚከሰተውን Mania የተሰኘ ችግር ለመቆጣጠር በደንብ የሚሰራ የታወቀ የስሜት ማረጋጊያ መድሐኒት ነው። ጥናቶች እንደሚያሳዩት ሊቲየም ለረጅም ጊዜ በሚጠቀሙ ሰዎች ላይ ራስን የማጥፋት አደጋን ይቀንሳል። ሀኪሞች ሊቲየም እየወሰዱ ያሉ ሰዎችን የሊቲየም መጠናቸውን፣ ኩላሊቶቻቸውን እና ታይሮይዳቸው እየሰራ መሆን አለመሆኑን እንዲመረመሩ በየጊዜው ይጠይቃሉ።

እነዚህ መድሃኒቶች ድባቴን፣ schizoaffective disorderን፣ disorders of impulse controlን እና በልጆች ላይ የሚከሰቱ አንዳንድ የአእምሮ ሕመሞችን ለመቆጣጠር ጥቅም ላይ ሊውሉ ይችላሉ። ሐኪሞች ባይፖላር ዲፕሬሽን ላለባቸው ሰዎች ድንገተኛ የስሜት ለውጦችን ለመከላከል የስሜት ማረጋጊያ እና ፀረ-ድባቴ መድሐኒቶችን ያዝዛሉ።

አንዳንድ Anti-convulsant መድሃኒቶች እንደ ስሜት ማረጋጊያ ሆነው ሊያገለግሉ ይችላሉ፤ በተለይ Manya እና ድባቴ ላለባቸው ሰዎች፤ ወይም የተቀላቀሉ ምልክቶች ወይም ቶሎ ቶሎ የሚከሰት ባይፖላር ዲስኦርደር ላለባቸው ሰዎች። anti-convulsant መድሐኒት የሚወስዱ ሰዎች መድሀኒቱ በሰውነታቸው የሚፈጥረውን ለውጥ፣ የጎንዮሽ ጉዳቶቹን እና ከሌሎች መድሃኒቶች ጋር የሚፈጥረውን ጉድኝት መደበኛ ህክምና መከታተል ያስፈልጋቸዋል።

This post is also available in: English (እንግሊዝኛ)