Skip to content

PTSD ምንድን ነው?

PTSD የሚለው ምህጻረ ቃል Post-traumatic stress disorder በመባል ይነበባል። አስደንጋጭ፣ አስፈሪ ወይም አደገኛ ክስተት ያጋጠማቸው አንዳንድ ሰዎች ከክስተቱ በኋላ የሚያጋጥማቸው የአእምሮ መታወክ PTSD ይባላል።

በማንኛውም እድሜ ላይ ያለ ማንኛውም ሰው  በPTSD ሊጠቃ ይችላል። አአሰቃቂ ሁኔታዎች በሚከሰቱበት ጊዜ እና ከክስተቱ በኋላ መፍራት እና መደንገጥ ተፈጥሯዊ ነው። ፍርሃት ድንገተኛ አደጋ ሲከሰት ሊደርስብን የሚችለውን ጉዳት ለመከላከል ወይም ለመቀነስ ሰውነታች ከሚሰጣቸው ተፈጥሯዊ ምላሾች አንዱ ነው። አሰቃቂ ሁኔታ ውስጥ ያለፉ ሰዎች ከክስተቱ በኋላ ብዙ የተለያዩ አንግዳ ስሜቶችን ሊያስተናግዱ ይችላሉ፤ አብዛኛው ሰው በጊዜ ሂደት ከዚህ ትሮማ እያገገመ ይሄዳል። ነገር ግን በጊዜ ሂደት እምብዛም ለውጥ ያላሳየ ሰው ችግሩ PTSD መሆን አለመሆኑን መመርመር አለበት።

የPTSD ተጠቂ ሊሆን የሚችለው ማነው?

ከጦርነት የተመለሱ ወታደሮች፣ አካላዊ ወይም ጾታዊ ጥቃት የደረሰባቸው ወይም ሲደርስ የተመለከቱ ሰዎች፣ ከመኪና አደጋ የተረፉ እና ሌሎች ከባድ ክስተቶች ያጋጠማቸው ወይም የተመለከቱ ማንኛውም ሰዎች የPTSD ተጠቂ የመሆን እድል አላቸው።

PTSD ያለበት ሰው ሁሉ በአሰቃቂ ክስተት ውስጥ ያለፈ አይደለም። አንዳንድ ጊዜ፣ ጓደኛ ወይም የቤተሰብ አባል ያለፈበትን አሰቃቄ ሁኔታ ማወቅ ብቻውን PTSD ሊያስከትል ይችላል።

የአሜሪካ የአርበኞች ጉዳይ ዲፓርትመንት ፕሮግራም የሆነው ብሔራዊ የ PTSD ማዕከል ባወጣው መረጃ መሰረት ከ100 ሰዎች ውስጥ ስድስት ያህሉ በሕይወታቸው ውስጥ በሆነ ወቅት PTSD ያጋጥማቸዋል። ሴቶች ለPTSD የመጋለጥ እድላቸው ከወንዶች ሰፋ ያለ ነው። የአሰቃቂ ክስተት አንዳንድ ገፅታዎች እና አንዳንድ ባዮሎጂካል ምክንያቶች (ለምሳሌ ዘረመል) የሰዎችን ለPTSD የመጋለጥ እድል ከፍ እና ዝቅ ሊያደርጉ ይችላሉ።

የ PTSD ምልክቶች ምንድናቸው?

የPTSD ምልክቶች አሰቃቂ ሁኔታው በተከሰት 3 ወር ጊዜ ውስጥ ይጀምራሉ፤ ነገር ግን አንዳንድ ጊዜ ከዛም ቆይተው ሊመጡ ይችላሉ። አንድ ሰው PTSD አለበት ለማለት ምልክቶቹ ከአንድ ወር ለበተለጠ ጊዜ ሊታዩበት ይገባል፤ እናም ምልክቶቹ በዕለት ተዕለት ሕይወት ውስጥ፥ ለምሳሌ ከሰዎች ጋር ባለን ግንኙነት  ወይም ሥራ ላይ፣ ጣልቃ እከመግባት እና እስከማደናቀፍ ድረስ የከበዱ መሆን አለባቸው። እንዲሁም የምልክቶቹ መንስኤ ከምንጠቀማቸው መድሃኒቶች፣ ከአደኝዛዥ እጽ ወይም ከሌሎች በሽታዎች ጋር ያልተያያዘ መሆን አለበት።

የሕመሙ አካሄድ እና ሁኔታ ከሰው ሰው ይለያያል። አንዳንድ ሰዎች በ6 ወራት ውስጥ ይፈወሳሉ፤ በሌሎች ላይ ደግሞ ምልክቶቹ ለ1 ዓመት ወይም ከዚያም በላይ ሊቆዩ ይችላሉ። PTSD ያለባቸው ሰዎች ብዙውን ጊዜ ድባቴ፣ የአደንዛዥ ዕፅ ሱሰኝነት እና አንድ ወይም ከዚያ በላይ የጭንቀት መታወክ ችግሮች ይታይባቸዋል።

አደገኛ ክስተቶች ከተከሰቱ በኋላ አንዳንድ ምልክቶች መኖራቸው ተፈጥሯዊ ነው። ለምሳሌ አንዳንድ ሰዎች በአንዳንድ ሁኔታዎች የሁኔታው አካል ሆነው ሳለ ነገር ግን ተመልካች እንደሆኑ ሊሰማቸው እና ከሁኔታው የመነጠል ስሜት ውስጥ ሊገቡ ይችላሉ። PTSD ያለባቸውን ሰዎች የመርዳት ልምድ ያላቸው የጤና ባለሙያዎች፣ ለምሳሌ ሳይካትሪስቶች፣ ሳይኮሎጂስቶች፣ እና መሰል ሀኪሞች ሰዎች ላይ የሚታዩ ምልክቶች የPTSD መሆን አለመሆናቸውን መወሰን ይችላሉ።

አንድ አዋቂ ሰው PTSD አለበት ለማለት የሚከተሉ ምልክቶች በሙሉ ቢያንስ ለ 1 ወር ሊታይበት ይገባል፦

  • ቢያንስ አንድ ያለፈን ክስተት እንደገና የመለማመድ ምልክት
  • ቢያንስ አንድ ከነገሮች የመሸሽ ምልክት
  • ቢያንስ ሁለት የመነቃቃት እና ምላሽ ለመስጠት ዝግጁ የመሆን ምልክቶች
  • ቢያንስ ሁለት የግንዛቤ እና የስሜት ምልክቶች

ያለፈን ክስተት እንደገና የመለማመድ ምልክት የሚከተሉትን ያካትታል:

  • ያለፈው አሰቃቂ ክስተት እንደገና እንደተከሰተ በማሰብ መደንገጥ እና ምላሽ ለመስጠት መዘጋጀት፤ ፈጣን የልብ ምት ወይም በላብ መጠመቅ በዚህ ወቅት የሚታዩ አካላዊ ምልክቶች ናቸው።
  • ከክስተቱ ጋር የተያያዙ ትውስታዎች እና ህልሞችን በተደጋጋሚ ማየት።
  • በተደጋጋሚ በአስጨናቂ ሀሳቦች መሞላት
  • ጭንቀትን የሚጠቁሙ አካላዊ ምልክቶችን ማሳየት

ክስተቱን የሚያስታውሱ ሁኔታዎች፣ ንግግሮች፣ ስሜቶች እና እቃዎች እነዚህን ምልክቶች ሊቀሰቅሱ ይችላሉ።

ከነገሮች የመሸሽ ምልክት የሚከተሉትን ያካትታሉ:

  • አሰቃቂውን ክስተት የሚያስታውሱ ቦታዎችን፣ ክስተቶችን ወይም ነገሮችን ማስወገድ ወይም ከነሱ መሸሽ።
  • ከአሰቃቂው ክስተት ጋር የተያያዙ ሀሳቦችን እና ስሜቶችን ማስወገድ ወይም ከነሱ መሸሽ።

ይህ ምልክት የሚታይባቸው ሰዎች የለመዱትን የውሎ ቅድመ ተከተል እስከመቀየር ሊሄዱ ይችላሉ። ለምሳሌ አንዳንድ ሰዎች ከባድ የመኪና አደጋን ተከትሎ መኪና መንዳትን ወይም በመኪና መሄድን ያቆማሉ።

የመነቃቃት እና ምላሽ ለመስጠት ዝግጁ የመሆን ምልክቶች የሚከተሉትን ያካትታሉ:

  • በቀላሉ መደንገጥ
  • የውጥረት፣ የአለመረጋጋት እና የፍርሃት ስሜት
  • ትኩረት ማድረግ አለመቻል
  • ከእንቅልፍ ጋር የተያያዙ ችግሮች
  • ብስጭት፣ ቁጣ ወይም ንዴት
  • ጥንቃቄ የጎደላቸው እና አደገኛ ተግባራት ላይ መሳተፍ።

የመነቃቃት ምልክቶች ብዙ ጊዜ የማይለዋወጡ ናቸው። የመነቃቃት ምልክቶች ብዙ ጊዜ ጭንቀት እና ንዴትን ያስከትላሉ። እንቅልፍ፣ ምግብ መብላት ወይም ስራዎቻችን ላይ ማተኮርን የመሳሰሉ የለት ተለት ህይወታችን ውስጥ ጣልቃ በመግባት ይረብሻሉ።

የግንዛቤ እና የስሜት ምልክቶች የሚከተሉትን ያካትታሉ:

  • የአሰቃቂውን ክስተት ቁልፍ ቁልፍ ክፍሎች ለማስታወስ መቸገር
  • ስለራስ ወይም ስለ ዓለም አሉታዊ አመለካከት ማዳበር
  • ራስን ወይም ሌሎችን በተጋነኑ መልኩ ጥፋተኛ ማድረግ።
  • ፍርሃት፣ ቁጣ፣ የጥፋተኝነት ስሜት፣ ሀፍረት እና በመሳሰሉ አሉታዊ ስሜቶች ለረጀም ጊዜ ሞሞላት።
  • አስደሳች በሆኑ ተግባራት ላይ ፍላጎት ማጣት
  • ከማህበረሰብ የመገለል ስሜት ማዳበር
  • ደስታ፣ እርካታ እና ከመሳሰሉ አዎንታዊ ስሜቶች መራቅ

የግንዛቤ እና የስሜት ምልክቶች ከአሰቃቂው ክስተት በኋላ ሊጀምሩ ወይም ሊባባሱ ይችላሉ። ግለሰቡን ከጓደኞች ወይም ከቤተሰብ አባላት እንደተገለለ እንዲሰማው ሊያደርጉት ይችላሉ።

እርእርስዎ ወይም የሚያውቁት ሌላ ሰው ራስን ስለማጥፋት በተደጋጋሚ የሚያስብ ከሆነ፣ ወደ 988 ይደውሉ ወይም የጽሑፍ መልእክት ይላኩ። ወይም በሚከተለው ድህረገጽ 988lifeline.org በመግባት ከባለሙያ ጋር በጽሑፍ ይወያዩ። ለሕይወት አስጊ በሆኑ ሁኔታዎች፣ ወደ 911 ይደውሉ።

ልጆች እና ታዳጊዎች አሰቃቂ ሁኔታ ከተከሰተ በኋላ ለሚያጋጥም የስነልቦና ቀውስ ወይም ትሮውማ ምን አይነት ምላሽ ይሰጣሉ?

ልጆች እና ታዳጊዎች አሰቃቂ ሁኔታ ከተከሰተ በኋላ ለሚያጋጥም የስነልቦና ቀውስ ወይም ትሮውማ እጅግ ከፍ ያለ ምላሽ ሊያሳዩ ይችላል፣ ነገር ግን እነሱ ላይ የሚታዩ አንዳንድ ምልክቶች በአዋቂዎች ላይ ከሚታዩት ጋር ተመሳሳይ ላይሆኑ ይችላሉ። ከ 6 ዓመት በታች በሆኑ ህጻናት ላይ የሚታዩ ምልክቶች የሚከተሉትን ሊያካትቱ ይችላሉ፦

  • ሽንት ቤት መጠቀምን የለመዱ ሆነው ሳለ ከትሮማው በኋላ ግን መኝታቸው ላይ መሽናት ሊጀምሩ ይችላሉ
  • ማውራት ሊረሱ ወይም መናገር ወደ አለመቻል ሊመጡ ይችላሉ።
  • በጨዋታ ጊዜ አስፈሪ ነገሮች ሊፈጽሙ ይችላሉ
  • ባልተለመደ ሁኔታ ከወላጃቻቸው ወይም ከአዋቂዎች ጋር መጣበቅ ወይም ማቀፍ ሊጀምሩ ይችላሉ።

ትላልቅ ልጆች እና ታዳጊዎች ብዙውን በአዋቂዎች ላይ ከሚታዩ ምልክቶች ጋር ተመሳሳይ ምልክት ያሳያሉ። ነገር ግን እነሱም የሚረብሹ፣ አክብሮት የጎደላቸው እና አጥፊ ባህሪያት ሊያመጡ ይችላሉ። ትልልቅ ልጆች እና ታዳጊዎች ጉዳትን ወይም ሞትን ባለመከላከላቸው የጥፋተኝነት ስሜት ሊሰማቸው ይችላል። የበቀል ሀሳብም ሊያዳብሩ ይችላል።

ልጆች እና ታዳጊዎች አደጋዎችን እና ሌሎች አሰቃቂ ሁኔታ ከተከሰተ በኋላ የሚያጋጥም የስነልቦና ቀውስ ወይም ትሮውማን እንዲቋቋሙ እንዴት መርዳት እንደሚቻል የበለጠ ይማሩ።

የPTSD አደጋዎች ምንድናቸው?

በአደገኛ ክስተት ውስጥ ያለፉ ሰዎች ሁሉ በPTSD ይጠቃሉ ማለት አይደለም- ብዙ ምክንያቶች ሚና ይጫወታሉ። ከእነዚህ ምክንያቶች መካከል አንዳንዶቹ ከክስተቱ በፊት፣ አንዳንዶቹ በክስተቱ ወቅት እና አኔዳንዶቹ ደግሞ ከክስተቱ በኋላ ያሉ ናቸው።

  • ላለፉ በተይም በህጻንነት ለተከሰቱ ሰቅጣጭ ልምምዶች እንደገና መጋለጥ
  • አካላዊ ጉዳት ወይም ሌሎች ሲጎዱ ወይም ሲሞቱ መመልከት
  • ለአደገኛና አስፈሪ ወይም ለረዳት አልባነት ስሜት መጋለጥ
  • በአደገኛ ክስተት ውስጥ ካለፉ በኋላ ምንም አይነት ማህበራዊ ርዳታ አለማግኘት
  • ከሚወዱትን ሰው በሞት በመለየት፣ ከፍተኛ ህመም እና ሰቆቃ በማስተናገድ ወይም በስራ ስኬት በማጣት ምክንያት ለሚፈጠር ከፍተኛ ጭንቀት መጋለጥ።
  • በቤትሰብ መኻል በአእምሮ ህመመ የተጠቃ ወይም ለአደንዛዥ እዝ ሱስ የተጋለጠ ሰው መኖር፤ ወይም ግለሰቡም ይዚህ አይነት ታሪክ ሲኖረው።

በPTSD የመጠቃት እድልን ዝቅ ሊያደርጉ የሚችሉ ምክንያቶች የሚከተሉት ናቸው።

  • ከጓደኞች፣ ከቤተሰብ ወይም ከድጋፍ ቡድኖች እርዳታን መፈለግ
  • ለተፈጠረው ለአሰቃቂ ክስተት የምንሰጠው ምላሽ ከተፈጥሮ የወጣ አለመሆኑን መገንዘብ እና አለመረበሽ
  • በአሰቃቂ ሁኔታ ውስጥ የምናልፍበትን እና ከሁኔታው የምንማርበትን ስልት መንደፍ።
  • አሳዛኝ ክስተቶች ሲከሰቱ ከመፍራት ይልቅ እንዴት ማስተናገድ እንደሚገባን መዘጋጀት እና በአግባቡ ለማስተናገድ ብቁ መሆን

PTSD እንዴት ይታከማል?

የPTSD ምልክት ያለበት ማንኛውም ሰው PTSDን የማከም ልምድ ካለው የአእምሮ ጤና ባለሙያ ጋር አብሮ መስራት አስፈላጊ ነው። ዋናዎቹ ሕክምናዎች ሳይኮቴራፒ እና መድኃኒት፣ ወይም የሁለቱ ጥምር ነው። የአእምሮ ጤና ባለሙያ ሰዎች ለምልክቶቻቸው እና ለፍላጎታቸው ተስማሚ እና ምርጥ የሆነውን የሕክምና ዕቅድ እንዲያገኙ ሊረዳቸው ይችላል።

አንዳንድ PTSD ያለባቸው ሰዎች፣ ለምሳሌ ጭቆና ያለበት ግንኙነት ውስጥ ያሉ ሰዎች፣ ቀጣይነት ባለው ትሮውማ ውስጥ ሊኖሩ ይችላሉ። በእነዚህ ሁኔታዎች ህክምና በጣም ውጤታማ የሚሆነው ትሮውማውን የPTSD ምልክቶችንም የሚዳስስ እና የሚያክም ሲሆን ነው። አሰቃቂ ሁኔታዎች ያጋጠማቸው ወይም PTSD ያለባቸው ሰዎች ድንገጤ እና ራስን መሳት፣ ድባቴ፣ አደንዛዥ እፅ መጠቀም ወይም ራስን የማጥፋት ሀሳቦች እና መሰል ችግሮች ውስጥም ሊገቡ ይችላሉ። ለእነዚህ ችግሮች የሚደረጉ ሕክምናዎች ከትሮውማ ለማገገም ይረዳል። ጥናቶች እንደሚያሳዩት ከቤተሰብ እና ከጓደኞች የሚደረግ ድጋፍ ለማገገም እጅግ አስፈላጊ ነው።

ሳይኮቴራፒ

ሳይኮቴራፒ (አንዳንድ ጊዜ የንግግር ሕክምና ተብሎ የሚጠራው) የአእምሮ ጤና ባለሙያዎች ሰዎች የሚያስጨንቁ ስሜቶችን፣ ሀሳቦችን እና ባህሪዎችን እንዲለዩ እና እንዲቀይሩ ለመርዳት የሚጠቀሙባቸውን የተለያዩ የሕክምና ዘዴዎችን ያጠቃልላል። ሳይኮቴራፒ PTSD ላለባቸው ሰዎች እና ለቤተሰቦቻቸው ድጋፍ፣ ትምህርት እና መመሪያ ሊሰጥ ይችላል። ሕክምናው አንድ በአንድ ወይም በቡድን ሊከናወን ይችላል፤ እናም አብዛኛውን ጊዜ ከ 6 እስከ 12 ሳምንታት ይቆያል፤ ነገር ግን ረዘም ላለ ጊዜ ሊቆይም ይችላል።

አንዳንድ የሳይኮቴራፒ ዓይነቶች የPTSD ምልክቶች ላይ ብቻ ያተኩራሉ። ሌሎች ደግሞ በማህበራዊ፣ ቤተሰብ ወይም ከስራ ጋር በተያያዙ ችግሮች ላይ ያተኩራሉ። ውጤታማ የሳይኮቴራፒ ሕክምናዎች ትሮማውን የሚቀሰቅሱ ነገሮችን ለመለየት እና ምልክቶችን በአግባቡ ለመቆጣጠር የሚረዱ የመማር ክህሎቶችን ጨምሮ ጥቂት ቁልፍ ክፍሎችን አጽንኦት ይሰጣል።

Cognitive behavioral therapy የሚባለው የተለመደ የሳይኮቴራፒ ዓይነት የተጋላጭነት ሕክምና እና የግንዛቤ ምህዋርን መልሶ ማዋቀርን ሊያካትት ይችላል።

  • የተጋላጭነት ሕክምና፣ ሰዎችን በጥንቃቄ እና በአስተማማኝ መንገድ በፊት ለደረሰባቸው ትሮውማ እንደገና በማጋለጥ ፍርሃታቸውን ቀስ በቀስ መቆጣጠርን እንዲማሩ የሚያደርግ ህክምና ነው። ሰዎች ስለደረሰባቸው ጉዳት እንዲያስቡ ወይም እንዲጽፉ ወይም ጉዳቱ የተከሰተበትን ቦታ እንዲጎበኙ ማድረግ አንዱ የተጋላጭነት ህክምና አካል። ይህ ቴራፒ PTSD ያለባቸው ሰዎች የሚታይባቸውን ጭንቀት የሚያስከትሉ መንስኤዎች እንዲቀንሱ ይረዳል።
  • የግንዛቤ ምህዋርን መልሶ የማዋቀር ቴራፒ ሰዎች ስለ ደረሰባቸው አሰቃቂ ክስተት እንደገና እውነተኛ እና ትክክለኛ በሆነ መንገድ እንዲያስቡ የሚረዳ ቴራፒ ነው። አንዳንድ ጊዜ ሰዎች የተፈጠረውን ክስተት ከክስተቱ በተለየ መኝገድ ያስታውሳሉ። የነሱ ጥፋት ባልሆነ ነገር የጥፋተኝነት ስሜት ሊሰማቸው ወይም ሊያፍሩ ይችላሉ። የግንዛቤን ምህዋር መልሶ የማዋቀር የማዋቀር ቴራፒ PTSD ያለባቸው ሰዎች ስለተፈጠረው ነገር እውነተኛ እና ትክክለኛ በሆነ መንገድ እንዲያስቡ ይረዳቸዋል።

መድሃኒቶች

የU.S የምግብ እና የመድሀኒት አስተዳደር (FDA) ሁለት የተመረጡ በSSRIs ጎራ የሚመደቡ የፀረ-ድባቴ መድሀኒቶች PTSDን ለማከምም እንዲያገለግሉ አጽቋል። SSRIs ሀዘን፣ ጭንቀት፣ ቁጣ፣ የስሜት መደንዘዝ እና መሰል የPTSD ምልክቶችን ለመቆጣጠር ሊረዳ ይችላል። ሐኪሞች PTSDን ለማከም SSRIs እና ሌሎች መድሃኒቶችን በማዋኸድ ከሳይኮቴራፒ ጋር አንድ ላይ ሊጠቀሙ ይችላሉ። አንዳንድ መድሃኒቶች የእንቅልፍ ችግርን፣ ቅዠትን እና መሰል የተወሰኑ የPTSD ምልክቶችን ብቻ ለማከም ሊረዱ ይችላሉ።

ሰዎች ለራሳቸው ተስማሚ የሆነውን መድሃኒት ወይም የመድሃኒት ጥምረት እና ትክክለኛውን ዶዝ ለማግኘት ከሀኪሞች ጋር አብረው መስራት አለባቸው። ስለ PTSD መድሐኒቶች የወጡ የቅርብ ጊዜ መረጃዎችኝ ለማግኘት የጤና ባለሙያዎችን ያማክሩ፤ እንዲሁም የFDAን ድረ-ገጽ ይጎብኙ።

ከPTSD ጋር በተያያዘ እርዳታ እንዴት ማግኘት እችላለሁ?

እርዳታ የት ማግኘት እንደሚችሉ ካላወቁ፣ የጤና ባለሙያ ጋር ይሂዱ እና ህጋዊ ፈቃድ ወዳለው የአእምሮ ጤና ባለሙያ ሊልክዎ ይችላል፤ ለምሳሊ PSTDን በማከም ልምድ ያለውን ሳይካትሪስት ወይም ሳይኮሎጂስት ሊጠቁምዎ ይችላል። ወደ ህክምና ተቋም ከመሄድዎ በፊት ስለ ህክምና ተቋማት ቅድመ ግኝዛቤ የሚያስጨብጡ ምክሮችን ያግኙ

የአደንዛዥ እጽ እና የአእምሮ ጤና አገልግሎት አስተዳደር ድረገጽን በመጠቀም በአካባቢዎ ያሉ የአእምሮ ጤና አገልግሎት ማእከላትን በቀላሉ ማግኘት ይችላሉ።

በህክምና ላይ እያሉ እራስዎን ለመርዳት ማድረግ የሚችሏቸው አንዳንድ ነገሮች እነሆ፡-

  • ከጤና እንክብካቤ አቅራቢዎ ጋር ስለ ሕክምና አማራጮች ይነጋገሩ፤ እንዲሁም የሕክምና ዕቅድዎን ይከተሉ።
  • በአካል ብቃት እንቅስቃሴ፣ በተመስጥኦ ወይም ሌሎች ጭንቀትን ለመቀነስ በሚረዱ ተግባራት ላይ ይሳተፉ።
  • ለምግብ፣ ለአካል ብቃት እንቅስቃሴ እና ለእንቅልፍ እቅድ አውጥተው በወጥነት ይከተሉ።
  • ማሳካት የሚችሏቸውን ግቦች ይንደፉ እና በቀየረሰ እና መቆጣጠር በሚችሏቸው ነገሮች ላይ ያተኩሩ።
  • ከሚያምኑት ጓደኛ ወይም ዘመድ ጋር ጊዜ በማሳለፉ ትሮማውን ስለሚቀሰቅሱ ነገሮች ከእነሱ ጋር ይነጋገሩ
  • ምልክቶቹ ወዲያውኑ ሳይሆን በጊዜ ሂደት ቀስ በቀስ እንደሚሻሻሉ ይጠብቁ።
  • አልኮል ወይም አደንዛዥ ዕፅ ከመጠቀም ይቆጠቡ።

PSDT ያለበትን ጓደኛ ወይም ዘመድ እንዴት መርዳት እችላለሁ?

PTSD ያለበትን ሰው የሚያውቁ ከሆነ እርስዎ ለዛ ሰው ማድረግ የሚችሉት በጣም አስፈላጊው ነገር ያ ሰው ትክክለኛውን ምርመራ እና ህክምና እንዲያገኝ መርዳት ነው። አንዳንድ ሰዎች ከጤና ባለሙያዎች ጋር ቀጠሮ በመያዝ መታከም ሊያስፈልጋቸው ይችላል። ሌሎች ደግሞ ወደ ህክምና ማዕከላት አብሮአቸው የሚሄድ ሰው በመኖሩ ብቻ ብዙ ሊጠቅሙ ይችላሉ።

የቅርብ ጓደኛ ወይም ዘመድ የPTSD በሽታ እንዳለበት በህክምና ከተረጋገጠ ሕክምናቸውን በአግባቡ እንዲከተሉ በማበረታታት ሊረዱት ይችላሉ። በሽታው ከ6 እስከ 8 ሳምንታት ወስጥ ካልተሻሻለ፣ ግለሰቡ የጤና ባለሙያዎችን እንዲያነጋግር በማበረታታት ሊያበረታቱት ይችላሉ። እንዲሁም የሚከተሉትን ማድረግ ይችላሉ፦

  • የስሜት ድጋፍ ያድርጉለት፤ ትዕግስት በማሳየት፣ በማበረታታት እና እንደተረዱት በማሳየት ከጎኑ መቆም ይችላሉ።
  • ጓደኛዎ ምን በምን አይነት ሁኔታ ውስጥ እያለፈ እንዳለ ለመረዳት ስለ PTSD ይማሩ።
  • በጥሞና ያዳምጡ። ለግለሰቡ ስሜት እና የPTSD ምልክቶችን ሊቀሰቅሱ ለሚችሉ ሁኔታዎች ትኩረት ይስጡ።
  • አብረውት ለእግር እርምጃ እና ለአንዳዱ ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች በመውጣት ያዝናኑት።

ለPTSD ክሊኒካዊ ሙከራ እንዴት ማግኘት እችላለሁ?

ክሊኒካዊ ሙከራ ማለት በሽታዎችን ለመከላከል፣ ለመመርመር ወይም ለማከም የሚረዱ አዳዲስ መንገዶችን ለማግኘት የሚደረግ የምርምር ጥናት ነው። የክሊኒካዊ ሙከራ ግብ አዲስ ምርመራ ወይም ህክምና እንደሚሰራ እና ደህንነቱም የተጠበቀ መሆኑን ማረጋገጥ ነው። ምንም እንኳን ሰዎች የክሊኒካዊ ሙከራ ተሳታፊ በመሆን ሊጠቀሙ ቢችሉም የክሊኒካዊ ሙከራ ዋና ዓላማ ግን በሽታውን የተሻለ ለመረዳት የሚያስችሉ አዳዲስ ሳይንሳዊ እውቀቶችን ማግኘት መሆኑን ማወቅ አለባቸው።

በNIMH ያሉ እና ሌሎችም ተመራማሪዎች ከበሽተኞች እና ጤነኛ ከሆኑ በጎ ፈቃደኞች ጋር በመሆን ብዙ ጥናቶችን ያካሂዳሉ። ከአመታት በፊት በተደረጉ ክሊኒካዊ ሙከራዎች ምክንያት፣ ዛሬ ላይ አዳዲስ እና የተሻሉ የሕክምና አማራጮች አሉን። ከጤና ባለሙያዎች ጋር ስለ ክሊኒካዊ ሙከራ፣ ስለ ጥቅም እና ጉዳቱ፣ እና እንዲሁም የክሊኒካው ሙከራ ተሳታፊ መሆን ትክክል ስለመሆን አለመሆኑ ይወያዩ።

የበለጠ ለማወቅ እና የዳሰሳ ጥናት ለማግኘት የሚከተሉ ድረገጾችን ይጎብኙ፡-

  • የNIMH ክሊኒካዊ ሙከራዎች ድህረ ገጽ፦ በክሊኒካዊ ሙከራዎች ውስጥ ስለመሳተፍ የወጡ መረጃዎች
  • Clinicaltrials.gov፡ ስለPTSD የተደረጉ ወቅታዊ ምርምሮች፡ በብሔራዊ የጤና ተቋማት (NIH) ገንዘብ ድጋፍ የተደረጉ ክሊኒካዊ ሙከራዎች በመላ አገሪቱ እየተካሄዱ ናቸው።

ከየት ነው ስለ PTSD የበለጠ ማወቅ የምችለው?

ነፃ ብሮሹሮች እና ሊጋሩ የሚችሉ መረጃዎች

  • ልጆችን እና ታዳጊዎችን ከአሰቃቂ ክስተቶች ጋር በተያያዘ በሚፈጠርባቸው ችግሮች መርዳት፡ ከስር ያለው የእውነታ ወረቀት ልጆች እና ታዳጊዎች ለአሰቃቂ ሁኔታዎች እንዴት ምላሽ እንደሚሰጡ እና ቤተሰብ፣ ጓደኞች እና የሚታመኑ አዋቂዎች እንዴት ሊረዷቸው እንደሚችሉ መረጃ ይሰጣል። ጽሑፉ በስፔንኛም ይገኛል።
  • Post Traumatic Stress Disorder: ይህ ብሮሸር PTSD ምን እንደሆነ፣ PTSDን ማን እንደሚስከትል፣ ስለ ምልክቶቹ፣ ስለ ሕክምና አማራጮች እና ለራስዎ ወይም PTSD ላለበት ሌላ ሰው እርዳታ እንዴት ማግኘት እንደሚቻል መረጃ ይሰጣል። በ ስፔንኛም ይገኛል።
  • Digital Sharing on PTSD: እነዚህ ዲጂታል ግብዓቶች፣ ግራፊክስ እና መልዕክቶችን የያዙ ሲሆን፣ ስለ PTSD መረጃ ለማሰራጨት እና ማህበረሰብን ግንዛቤ ለማስጨበጥ ይረዳሉ።

መልቲሚዲያ

  • NIMH-Funded Researcher Discusses PTSD: በዚህ ቪዲዮ አንድ የዘርፉ ተመራማሪ ስለPTSD ምልክቶች፣ ህመሞች፣ ስለ ምርመራው፣ ህክምናው እና PTSD ላይ ስለ ተደረጉ የቅርብ ጊዜ ምርምች ማብራርያ ይሰጣል።

የፌዴራል ሀብቶች

  • National PTSD Center: ይህ ማዕከል የU.S የአርበኞች ጉዳይ አካል ሲሆን፣ ይህ ድህረ ገጽ ስለ PTSD ለማወቅ ፍላጎት ላለው ማንኛውም ሰው መረጃ እና ግብዓቶች ያቀርባል፤ ይህም የቀድሞ ወታደሮችን፣ ቤተሰብን፣ ጓደኞችን፣ ተመራማሪዎችን እና የጤና እንክብካቤ አቅራቢዎችን ያጠቃልላል። ድረ ገጹ PTSD ያለባቸውን እና ቤተሰቦቻቸውን የሚረዱ ቪዲዮዎች፣ መተግበሪያዎች፣ የኢንተርኔት ፕሮግራሞችን እና ሌሎች መሣርያዎችንም ይዟል።
  • Medications for PTSD: ይህ ድረ-ገጽ የU.S አርበኞች ጉዳይ ዲፓርትመንት አካል ሲሆን PSDTን ለማከም ስለሚረዱ ውጤታማ መድሃኒቶች እና የሕክምና አማራጮች ዝርዝር መረጃ ያቀርባል።
  • PTSD (Medline Plus – also en Español)

https://www.nimh.nih.gov/health/topics/post-traumatic-stress-disorder-ptsd

This post is also available in: English (እንግሊዝኛ)

Index